የሀገር ውስጥ ዜና

አምስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀናት በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን ሰርተዋል

By Meseret Awoke

November 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ፍራንስ 24 የተሰኙ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን መልቀቃቸው ታውቋል።

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ የሚተላለፈው የ”ቴክቶክ” ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ካሳ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ ÷ ምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙኃን ሆን ብለው በህዝቡ ውስጥ ሽብር ለመፍጠር የሀሰት ዘገባዎችን በስፋት እያሰራጩ ናቸው ብሏል።

ዛሬም የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በህይወት አለ ያለው ሰሎሞን ÷ ከሰሞኑ የሚሰራጩት ሀሰተኛ ዘገባዎች ዋና አላማም አዲስ አበባ በሽብር ቡድኖች እንደተከበበች በማስመሰል ሽብር መንዛትና ሥነ ልቦናዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው ብሏል።

በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ሰልፍ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጩትን የሀሰት ዘገባ በማውገዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!