Fana: At a Speed of Life!

በትናንትናው ዕለት ሴት ልጅ የተገላገለችው ተማሪ የ12 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየወሰደች ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው እለት ሴት ልጅ የተገላገለችው የሸዋሮቢት አጠቃላይ 2ኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳራ ሽመልስ የ12 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየወሰደች ነው።
 
በአማራ ክልል ሸዋሮቢት ከተማ የሸዋሮቢት አጠቃላይ 2ኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።
በትምህርት ቤቱ 775 መደበኛና 11 የግል ተፈታኞች ብሄራዊ ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
 
ከትምህርት ቤቱ ተፈታኞች መካከል በትናንትናው እለት ሴት ልጅ የተገላገለችው ተማሪ ሳራ ሽመልስ ትገኛለች።
 
ተማሪ ሳራ በጥሩ ጤንነት ላይ ሆና በዛሬው እለት ፈተናውን እየወሰደች መሆኑን ገልፃለች።
 
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎችም ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
 
በአላዩ ገረመው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.