የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ በአፋር ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

November 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጉምሩክ ኮሚሽን በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እንዲሁም ለአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ÷የጉምሩክ ኮሚሽን በክልሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ባጋጠመ ወቅት ተከታታይ ደጋፎች ማድረጉን ገልጸው በህልውና ዘመቻውም እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ በአፋር ህዝብ ልብ ውስጥ ለዘላለም እንደሚኖር ጠቅሰዋል፡፡