Fana: At a Speed of Life!

ከብክነት በጸዳ ሁኔታ የመኸር ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ምክክር እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይቱ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ÷ ይህ ጊዜ ሁሉንም ነገር በየዋህነት የምንመለከትበት ጊዜ አለመሆኑን ሁኔታዎች እየነገሩን ነው ተብሏል።

በመሆኑም እንደ ህወሓትና ሸኔ ያሉ ሽብርተኛ ቡድኖችን ነቅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊው አቶ ኡስማን ሱሩር ÷ አንዳንድ የዉጪ ሀይሎች በእኛ ላይ ያላቸው አቋም ምን እንደሆነ አውቀናል ብለዋል።

እነዚህ ሃይሎች ያላቸው ፍላጎት ምን እንደሆነ ጠንቅቀን ማወቅ አሸባሪ ሀይሎቹን ከስር ነቅሎ ለመጣል ወሳኝ አቅም አለን ያሉት አቶ ኡስማን ÷ ሀገር ካለ ሁሉም ነገር በጊዜው መልስ ያገኛልና መተባበርና ለአንድ አላማ መቆም ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

እኛ የግብርናው ዘርፍ አካላት የጦር ሰራዊቶች መሆናችንን አዉቀን ÷ አንድ ፍሬ ስንዴን እንደ አንድ ጥይት ቆጥረን የመኸር ስራችን ከብክነት የፀዳ እንዲሆን ለባለሙያው ድጋፍ ማድረግና ስራዎቻችንን ሁሉ ‘በጊዜ የለንም ቅኝት’ ማከናወን ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።

ህዝብ ማንቃት፣ በግንባር መሰለፍ፣ ለሰራዊቱ የሚደረገውን ድጋፍ ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ ኡስማን ሱሩር አሳስበዋል።

ተወያዮቹም ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር እስከ ግንባር የመዝመት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በመቅደስ አስፋው

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.