Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የነፃ ቪዛ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ እና የኢኳቶሪያል ጊኒው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሞን ኦዮኖ ተፈራርመውታል።

ይህም የዲፕሎማቲክ እና የአገልግሎት ፓስፖርት የያዙ ዜጎች ያለ ቪዛ መግባት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

ሚኒስትሮቹ ከስምምነት ፊርማው ባለፈ ባደረጉት ውይይት፥ የሃገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮችና ከዚህ በፊት የተፈረሙ ስምምነቶችን አፈጻጸም በተመለከተ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት፥ በቱሪዝም እንዲሁም በነዳጅ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታዋ ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጅዩን ምባሌ ጋር መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.