የሀገር ውስጥ ዜና

በሀረሪ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል

By Feven Bishaw

November 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው እለት ፈተናው መሰጠት ተጀምሯል ሲል ገልጿል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ፈተናው እንዳይስተጓጎል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡