Fana: At a Speed of Life!

አንድነታችንን በማጠናከር የሕወሓትና ሸኔን ሴራ እናከሽፋለን – የጎፋ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎፋ ዞን ነዋሪዎች አሸባሪዎቹን ሕወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደግፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው “ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ያላትና የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌትና ኩራት ናት ብለዋል።
እኛ ኢትዮጵያውያን የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተልና አንድነታችንን በማጠናከር የአሸባሪዎቹን የሕወሓትና ሸኔን ሴራ እናከሽፋለንም ነው ያሉት።
የሚያጋጥሙንን ጊዜያዊ ፈተናዎች በመቋቋም የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በማስከበር ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
የሰልፉ ታዳሚዎች በበኩላቸው÷ አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ ለማክሸፍ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የትም፣ መቼም እና በምንም ሁኔታ ለሀገራችን እንዘምታለን ብለዋል፡፡
ሰልፈኞቹ በፕሮፓጋንዳው ጦርነት አንበገርም፣ ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን አይደናቀፍም፣ ክብር ለጀግናው መከላከያችንና ለመላው የፀጥታ ኃይላችን፣ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በሕዝባዊ ቁጭትና ጽናት ተሰልፈናል የሚሉና ሌሎችም የሽብር ቡድኖቹን ሕወሓትና ሸኔን የያወግዙ መልዕክቶች አስተጋብተዋል፡፡
የውጭ ሚዲያዎች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያወግዙ እንዲሁም ጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ የተለያዩ መፈክሮች መደመጣቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.