የኮንፌደሬሽን ጥምረት ፈጥረናል ብለው ብቅ ያሉ የህወሓትደጋፊዎችን ጥምረቱ አይቀበልም – የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በአሜሪካ በህወሓት መሪነት በኮንፌደሬሽን ጥምረት ፈጥረናል ብለው ብቅ ያሉ ሃይሎች ተግባር እንደሚያወግዝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።
የዛሬ አመት ህወሓት በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት አገርን ለዛሬ ቀውስ ዳርጓል ያለው ምክርቤቱ የውጭ አገራት መንግስታትና ግለሰቦች አሻንጉሊት መንግስት ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት የለውም ነው ያለው።
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ላይ የሚሰራውን ስራ አገራት ቆም ብሎ ከመመልከት ይልቅ ለእኔም አይቀርም በሚል ሊንቀሳቀሱ እንድሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱ በመረጠው የሚተዳደረር እንጅ ተጠፍጥፎ በሚጫንበት መንግስት የመተዳዳር ታሪክ የለውም ብሏል።
በዚህም ማንኛውንም አይነት ጥምረት አንቀበልም ሲል አቋሙን ገልጿል።
የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመግለጫው ÷ ሁሉም ዜጋ በተለይ የውትድርና ልምድ ያላቸው አገራቸውን እንዲጠብቁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም ርብርብ እንዲደረግ እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ አፈፃፀሙ ላይ ከሰብአዊ መብት በተቃረነ አግባብ ማንነነትን መሰረት አድርጎ ዜጎች ላይ እንግልት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ይደረግ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪም አገራዊ መግባባት እንዲፋጠን መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!