Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር ግንባር ለሚገኘው ሕዝባዊ ሠራዊትድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር ግንባር በመፋለም ላይ ለሚገኘው ሕዝባዊ ሠራዊት1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የማኅበሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኀላፊ ሀበነ አበበ እንደገለጸው÷በአዲስ አበባ ከሚኖሩ ነዋሪዎች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ ግምቱ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚሆን ምግብ እና አልባሳት ግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ሕዝባዊ ሠራዊት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 
በቀጣይም የሽብር ቡድኑ እስኪደመሰስ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ግንባር በመሰለፍ ለመፋለም መዘጋጀታቸውን ገልጿል፡፡
 
ከዚህ በፊትም ወጣቶች ከአማራ የጸጥታ ኀይል ጋር በመቀላቀል የሽብር ቡድኑን እየተፋለሙ እንደሚገኙ ነው ወጣት ሀበነ የተናገረው፡፡
 
ማኅበሩ ከዚህ በፊትም በክልሉ የተለያዩ ችግሮች ባጋጠመበት ወቅት ከ19 ጊዜ በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስረድቷል፡፡
 
የአማራ ልዩ ኀይል ፖሊስ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ክፍል ምክትል ኀላፊ ኮሎኔል ጋሻው አባተ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አሸባሪውና ወራሪው የህውሓት ኀይል የሚያደርሰውን ጥፋት ለመቀልበስ በሚደረገው ትግል የደጀኑ ሕዝብ የስንቅ እና የሞራል ድጋፍ ትልቅ አቅም መፍጠሩን አንስተዋል፡፡
 
ወጣቱ ከሚያደርገው የስንቅ እና የሞራል ድጋፍ ባሻገር በሀገሪቱ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ በጀግንነት እየተፋለመ እንደሚገኝም ነው ኮሎኔሉ ያነሱት፡፡
 
የአማራ ወጣት ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመቀናጀት የውጭ ወራሪን እና የሀገር ውስጥ ባንዳን ድል በማድረግ የሀገሩን ነፃነት ያስከበረ በመኾኑ አሁንም አንድነቱን በማጠናከር የተቃጣበትን አደጋ እንዲመክት ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.