ከድል ዜና ጠባቂነት ተላቀን ወደ ድል አድራጊነት እንሸጋገራለን-የሃረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከድል ዜና ጠባቂነት ተላቀን ወደ ድል አድራጊነት እንሸጋገራለን ሲል የሃረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።
የጋራ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት የገባችው ፈልጋ ሳይሆን ተገዳ እና ሰላምን ለማምጣት በመሆኑ ዋጋ ለመክፈል ተገደናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዘመናት አንዳንድ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ሲፈትኗት የኖረች እና ያጋጠሟትንም ፈተናዎች በጀግና ልጆቿ መቀልበስ የቻለች አገር መሆኗን መግለጫው አውስቷል፡፡
ከአሸባሪው ትህነግ ጀርባ የመሸጉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ድብቅ ጦርነት በመክፈት ሃገራችን ከድህነት አረንቋ ለመውጣት የምታደርገውን ሁለንተናዊ ጥረት ለማደናቀፍ ጦርነት የከፈቱ ቢሆንም አይሳካም ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ኢትዮጵያውያን ከሁሉም ነገር በፊት አገርን አስቀድመን የገጠመንን ፈተና በድል እንወጣለን ማለታቸውን ከሃረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከድል ወይም ከምስራች ዜና ጠባቂነት ተላቀን እራሳችንን ወደ ድል አድራጊነት እናሸጋግራለንም ነው ያሉት ፓርቲዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!