የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  መደበኛ ስብሰባውን  ነገ ያካሂዳል

By Feven Bishaw

November 08, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ  በሚያካሂደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ  ኮሚቴ  አባላትን ለመሰየም  የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ  መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች  እጩ አመራርና  አባላትን  ምደባ  አስመልክቶ  እንዲሁም የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች  አደረጃጀት እና ተግባርና ሀላፊነት  ለመወሰን  የሚቀርብለትን የውሳኔ ሀሳብ  መርምሮ ያፀድቃል፡፡