Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ጦርነት ነው እየተዋጉ ያሉት” – የዩጋንዳ ጋዜጠኛ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀገራቸውን ብቻ ሳይሆን መላ አፍሪካን ከአሜሪካ የአዕምሮ እና የአካል እስራት ነፃ ለማውጣት አዲሱን ትግል እየመሩ እንደሚገኙ ዩጋንዳዊው ጋዜጠኛ  ገለጸ፡፡

በአፍሪካ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ፊውቸሪካል የተባለ የዩጋንዳ ዘጋቢ ጋዜጠኛ እንዳለው÷ አፍሪካን ከአሜሪካ የእስር ሰንሰለት ነፃ ለማውጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጎን ተሰልፈን እየታገልን ነው ብሏል።

አያይዞም ኩሩ፣ የበለፀገች እና ሰላማዊ የሆነች አህጉር ትኖረን ዘንድ በጋራ እንታገል ሲል  በማህበራዊ ትስስር ገጹ ጽፏል።

በሌላ የትዊተር መልዕክቱ ደግሞ ፥ “ ምናልባት ይህን ጉዳይ አሁን ላናደንቀው እንችላለን፤ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ጦርነት እየተዋጉ ነው ያሉት ሲል ገልጿል።

የአፍሪካ መግቢያ በር በኢትዮጵያ በኩል መሆኑን አሜሪካኖች ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ኢትዮጵያን ማንበርከክ ከቻልን፥ ቀሪዎቹ ከዋሽንግተን በተላከ አንድ የቃል ትዕዛዝ ይንበረከካሉ ብለው ነው የሚያምኑት፤ ስለዚህም ነው ኢትዮጵያን እየተዋጉ ያሉት” ብሎ የጻፈው።

ጋዜጠኛው ቀደም ሲል አስተያየት፥ በአማፅያን ተከባለች ተብሎ በእነሲ ኤን ኤን በተፃፈባት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች የሆኑ ባልደረቦቼን በማግኘቴ ኩራት ይሰማኛል ሲል የገለጸው ዩጋንዳዊው ጋዜጠኛ ፥ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ከሚያቀርቡት ዘገባ በተፃራሪ የአዲስ አበባን ዕውነታ ለመመስከር በመቻሌ የበለጠ ደስተኛ ነኝ ብሎም ነው የጻፈው።

“ አፍሪካ ውስጥ ከውጭ የሚነዛ ፕሮፖጋንዳ ቦታ እንዳይኖረው ለማድረግ፥ እኛ የአፍሪካ ጋዜጠኞች የአፍሪካን ዕውነታ የሚያንፀባርቁ አፍሪካዊ ታሪኮችን መዘገብ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ጋዜጠኞችን ማፍራት አለብን” ሲል አሳስቧል።

“ እኔ ኢትዮጵያን እደግፋለሁ፥ ምክንያቱም ነፃና ሉዓላዊ ሀገር በመሆኗ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እደግፋለሁ፥ ምክንያቱም በዴሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ የተመረጡ መሪ በመሆናቸው።

ኢትዮጵያውያንን እደግፋለሁ፥ ምክንያቱም ሰላምና አንድነት- አፍቃሪ ህዝቦች በመሆናችው።“ በማለት ዩጋንዳዊው ጋዜጠኛ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት መልዕክቱን አስተላልፏል።

በተመሳሳይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ባለሙያና በሙያው ተሸላሚ የሆነው ያገሩ ልጅ ዳንኤል ሉታያ፥ ሰሞኑን እዚሁ በመዲናችን ተገኝቶ የሲኤን ኤንን ሀሰተኛ ዘገባዎች ማጋለጡ ይታወሳል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.