Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ መሰጠት የተጀመረው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ቀንን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም÷ ፈተናው በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸው÷ ፈተናውም፣ በማንም፣ በምንም፣ በየትም አልተሰረቀም ብለዋል፡፡
2 ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል፣ 2 ተማሪዎች በደቡብ ክልል በስልካቸው ፎቶ አንስተው ”ኤሌክትሮኒክ ኩረጃ” ሊፈጽሙ ሲሉ መያዛቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
ተማሪዎቹ ወደ ፈተና ክፍል ከገቡ በኋላ÷ ፈተናውን በፎቶ አንስተው ሲላላኩ መያዛቸውን አንስተዋል፡፡
ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ከፌደራል ጀምሮ እስከታች ባሉ የኮማንድ ፖስቱ አባላት የተደረገው አስተዋጽኦ የተሻለ መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰሩ÷ በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ትብብሩ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡
ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተማሪዎች የሞባይል፣ የስማርት ሰዓትም ሆነ ሌሎች ዲጂታል ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ይዘው መግባት እንደማይፈቀድላቸው በመግለጫው አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡
በኃይለየሱስ ስዩም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.