Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ጠላቶቿን አሸንፋ የአፍሪካ ፈርጥና ምሳሌ ትሆናለች – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ጥንቱ ጠላቶቿን አሸንፋ የአፍሪካ ፈርጥና ምሳሌ ትሆናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሱ ሰዎች ህይወታቸውን ገብረው ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ ከሆነ ህይወታችንን ገብረን ኢትዮጵያን እናቆያታለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት ነው ለሚሉ ሰዎች “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግሉ ጀልባ ላይ ነውያለው፤በእያንዳንዱ ማዕበል መካከል ነው ያለው፤ ህዝቡን፣ሰራዊቱን፣የአገር ሽማግሌዎችን፣ሴቶችን ሁሉ አስተባብሮ ነጻ የተረከባትን አገር ለትውልድ ነጻ አገር ያስረክባል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የተነሱ በዚህ ግቡ፥ በዚህ ውጡ የሚሉ ሀይሎች፣ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ይሸነፋሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተባበረው ሃይል፣ኢትዮጵያን ለመዋጥ የተነሳው ዘንዶ በርቀት ሳይሆን በቅርብ ተወግቶ አንደሚፈርስና በአንጻሩ ኢትዮጵያ ለምልማና ባንዲራዋ ከፍ ብሎ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ አስታውቀዋል።
እጅግ ውስብስብ ፈተና ቢኖርብንም ማእበሉ የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍለን ኢትዮጵያን ወደ ሚገባት ሰላምና ብልጽግና እናስፈነጥራታለን ሲሉም ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People reached
3
Engagements
Distribution score
Boost post
3
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.