Fana: At a Speed of Life!

የስልጤ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት አራተኛ ዙር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስልጤ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ13 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ።

ዞኑ ለአራተኛ ጊዜ 323 ሰንጋዎችን፣ 36 በግና ፍየል ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ÷የክልሉ መንግስት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያቀረበውን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ የስልጤ ዞን ህዝብ ለሰራዊቱ ያደረገው ድጋፍ በክልሉ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዞኑ ህዝብ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 323 ሰንጋዎች፣ 36 በግና ፍየል እንዲሁም221 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ጠቁመዋል።

በክልሉ 500 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሸናፊ ሀሳብ ይዛ እስከተነሳች ድረስ የገጠማትን ፈተና በድል አድራጊነት ትወጣለች ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር በሀገሪቱ የተቃጣውን ወረራ ለመመከት በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ያለውን መከላከያ ሰራዊትን ማጠናከር ከምንም በላይ ትኩረት እንደተሠጠው አንስተው የዞኑ ህዝብ ለሰጠው ፈጣን ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.