Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ለመስራት ተዘጋጅቷል-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠዉ የኢትዮጵያ መንግስት በተጀመረዉ የለዉጥ ጉዞ ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ገንቢ በሆነ መልኩ ለመስራት መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ።

በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነውም ብለዋል።

መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.