ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን አልፋ ሠላሟን የማስፈን አቅም አላት ብለን እናምናለን – በተ.መ.ድ የቻይና አምባሳደር
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያን በውጪም በውስጥም ያጋጠሟቸውን ልዩነቶች ፈትተው የሀገራቸውን ሠላም በማስፈን ወደ ቀድሞ የተረጋጋ ማንነቷ ይመልሷታል የሚል ዕምነት አለን ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የቻይና አምባሳደር ዣንግ ጁን ገለጹ።
አምባሳደር ዣንግ ጁን ÷ ኢትዮጵያ የጥበበኞችና አቅም ያላቸው ዜጎች ሀገር ናት ብለዋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ፈታኝ ሁኔታም ውስጥ ዜጎቿ አንድነታቸውን ጠብቀው ይቆማሉ የሚል እምነት አለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደሩ ኢትዮጵያዊያን በውጪም በውስጥም ያጋጠሟቸውን ልዩነቶች ፈትተው የሀገራቸውን ሠላም በማስፈን ወደ ቀድሞ የተረጋጋ ማንነቷ ይመልሷታል የሚል ዕምነት አለንም ብለዋል፡፡