Fana: At a Speed of Life!

በአዋጁ ትግበራ በተደረገ ክትትል 237 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በተደረገ ጥብቅ ክትትል 237 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሣያስ አሸባሪው ህወሓትና ሸኔ ሀገር በማፍረስ ሴራ መጠመዳቸውን ጠቅሰው÷ ቡድኖቹን ለመመከት ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የፀጥታ አካላት ጭምር በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ያነሱት ኮሚሽነሩ÷ እነዚህ ተጠርጣሪዎች የሽብር ቡድኑን በገንዘብ፣ በሞራል፣ በሀሳብና መረጃ በማቀበል ሲረዱ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡

46 የጦር መሳሪዎች መያዛቸውን ጠቅሰው፥ አካል ጉዳተኛ በመምሰል የሽብር ቡድኑን ዕኩይ ተልዕኮ የያዙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

ማንኛውም ግለሰብ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ እንዳለበት እና የጦር መሳሪያ ያለው ግለሰብም ማስመዝገብ እንዳለበትም ማሳሰባቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.