Fana: At a Speed of Life!

የጃዊ ወረዳ ፋኖ አባላት የክተት ጥሪውን በመቀበል ወደ ግንባር ዘመቱ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃዊ ወረዳ ፋኖ አባላት የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የክተት ጥሪ በመቀበል ወደ ግንባር እየዘመቱ ነው።
 
ዘራፊውንና አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የጃዊ ወረዳ ፋኖ አባለት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
 
በሽኝት ፕሮግራሙ የፋኖ አባላት በመንግስት አደረጃጀት በመካተት የጠላትን ሃይል ለመደምሰስና ለመፋለም መወሰናቸው ተገልጿል።
 
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ደኛው÷የአማራ ክልል መንግስት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ በመቀበል በዞኑ የታጠቁ የሚሊሻ አባለት ወደ ግንባር እየዘመቱ መሆናቸውን አንስተዋል።
አሸባሪውን ሙሉ በሙሉ ደምስሰውና ከኢትዮጵያ ምድረ ገፅ አጥፍተው በትልቅ ጀብዱ ድል እንዲመለሱ ለፋኖ አባለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
ዘማች የፋኖ አባላት በበኩላቸው የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን ህወሓት ከአማራ ክልል ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ዳግም የኢትዮጵያ ዜጎች ስጋት እንዳይሆን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
ሁሉም ዜጎች የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ወደ ክተት ጥሪ እንዲቀላቀሉና አካባቢውን በንቃት እንዲጠበቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዊ ዞን ከሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.