Fana: At a Speed of Life!

ተማሪዎች ለሕዝባዊ ሠራዊቱ ስንቅ እያዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች አሸባሪና ወራሪውን ህወሓት እየተፋለመ ለሚገኘው ሕዝባዊ ሠራዊት ወገንተኝነታቸውን ለማሳየት ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ተማሪዎቹ በሰላም እንዲማሩ እና የሀገር ሕልውና እንዲጠበቅ የሕይዎት ዋጋ እየከፈለ ላለው ሕዝባዊ ሠራዊት በሚችሉት ሁሉ ለማገዝ እና ከጎኑ ለመቆም መነሳታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
 
የ8ኛ ክፍል ተማሪው አብቦ ድረስ ኢትዮጵያ ከተደቀነባት አደጋ እንድትወጣ ሕዝባዊ ኀይሉ ከጠላት ጋር እየተዋደቀ እንደሆነ እንደሚገነዘብ ተናግሯል።
 
ከሕዝባዊ ኃይሉ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ስንቅ እያዘጋጁ እንደሆነ አስረድቷል፡፡
 
ሌላኛዋ ተማሪ የትምወርቅ አድማሱ “ሠራዊቱ ወደ ግንባር የዘመተው እኛንና ሀገራችንን ለመጠበቅ እስከሆነ ድረስ እኛም አጋርነታችንን ለማሳየት ስንቅ እያዘጋጀን ነው” ብላለች፡፡
 
የእድገት ፈለግ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምሕርት ቤት ርዕሰ መምህር ታከለ ዘገየ÷አንድም ለሠራዊቱ ድጋፍ ለማድረግ ሁለትም ለተማሪዎቹ በተግባር የተደገፈ የሀገር ፍቅርን ማስተማር ዓላማ ያደረገ ሥራ መሠራቱን አንስተዋል፡፡
 
በሥራው ላይም ተማሪዎችን በማስተባበር እና በማገዝ የትምሕርት ቤቱ መምሕራን እና አስተዳደር ሠራተኞች መሳተፋቸውን አንስተዋል፡፡
 
በተማሪዎች የስንቅ ዝግጅት ሲከናወን የተመለከቱት የጎንደር ከተማ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ወይዘሮ እናትነሽ ዋለ ተማሪዎቹ ለወገን ኀይል የሚያደርጉት የስንቅ ዝግጅት እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
 
ተሞክሮው በሌሎች ትምሕርት ቤቶችም መስፋት እንዳለበት ነው የተናገሩት።
 
መምሪያ ኀላፊዋ አሸባሪው የትግራይ ኃይል አማራን አንገት ለማስደፋት የሚያደርገውን ወረራ ለመቀልበስ እና ለመደምሰስ ተማሪዎች እና መምሕራን እያደረጉ ያሉት የስንቅ ዝግጅት ትልቅ ትርጉም እንዳለው ማስገንዘባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡
 
የእድገት ፈለግ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምሕርት ቤት ተማሪዎች አዋጥተው ከሚያዘጋጁት ስንቅ በተጨማሪ ከወላጆቻቸው ጋር በመነጋገር የአንድ ቀን ቁርሳቸውን ሂሳብ ብስኩት በመግዛት ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.