የሀገር ውስጥ ዜና

የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸደቀ

By Meseret Awoke

November 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባ 11 አባላት ያሉት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል፡፡

በውሳኔ ሃሳቡ የቀረቡት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባዔ የመንግስት ተጠሪ ፣ ሚኒስትሮች፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ከገዥው ፓርቲ የተወከሉ የምክር ቤት አባላትን አካቷል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት ተግባርና ሃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

የጸደቀው የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች 11 አደረጃጀት ያለው ሲሆን ÷ በስራቸውም እያንዳንዱ ከ9 እስከ 13 አባላትን የሚይዝ ነው፡፡

ለእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴም ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢን ጨምሮ የኮሚቴ አባላት ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በሃይለኢየሱስ ስዩም

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!