Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳንበገር ተፈትነን አገራችንን እናሻግራለን – የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት የጥፋት ድርጊትና የሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይበግራቸው ተፈትነው አገርን ለማሻገር የድርሻቸውን እንደሚወጡ በድሬዳዋ ኢዜአ ያነጋገራቸው የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ገለጹ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ2 ሺህ 400 በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናቸውንተረጋግተው እየወሰዱ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

ተፈታኞቹ ኮሮና እና አሸባሪው ህወሓት ወቅታዊ ችግሮች ቢሆኑም ፈተናውን ተረጋግተው እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሓትና ተላላኪዎቹ ሀገር ተረካቢውን ትውልድ ለማምከን የሚያካሂደው ተስፋ የማስቆረጥ ተግባር በምንም መንገድ እንደማይሳካም ነው የገለጹት።

አሸባሪው ህወሓት አገርን ለማፍረስ እየፈጸመ ያለውን የጥፋት ድርጊት ያወገዙት ተፈታኞቹ፥ ቡድኑ በሚፈጽመው የጥፋት ድርጊትና በሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይበገሩ ተፈትነው አገርን ለማሻገር የድርሻቸውን እንደሚወጡም አስታውቀዋል።

አገርን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን የጥፋት ድርጊት ለመመከት ባላቸው አቅም በመሳተህ አገራቸውን ለማሻገር እንሚሰሩም ተናግረዋል።

ለሠራዊቱ ደም በመስጠትና የወያኔን ተላላኪዎች አጋልጦ ለህግ በመስጠት አካባቢያቸውን እንደሚጠብቁም አመላክተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.