Fana: At a Speed of Life!

የባህር የባህር ዳር ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በዘንዘልማ ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

የህብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍስሃ ወንድይፍራው ፥ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን መደገፍ ወገናዊ ግዴታ ነው።

እነዚህ ዜጎች አሁን የገጠማቸው ማህበራዊ ቀውስ እስኪፈታ ድረስ፣ አቅሙ ያለው ሁሉ መተባበርና ችግራቸውን በመጋራት ይህን አስቸጋሪ ወቅት ማሳለፍ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ህብረቱ ከዚህ ቀደምም ከ180 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የብርድ ልብስ፣ የምግብ ዘይትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በመጠለያ ጣቢያው ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅትም በመጠለያ ጣቢያው የሚስተዋሉ ችግሮችን መሰረት በማድረግ 350 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ እህልና ሌሎች ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አቶ ፍስሃ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተደረገው ድጋፍ የምግብ ዘይት፣ በርበሬ፣ ማካሮኒ፣ ሽሮ እንዲሁም የማገዶ እንጨትን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ከሰሜን ወሎ ዞኖች ተፈናቅለው ዘንዘለማ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ወገኖች ወደቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ ህብረቱ በፀሎት ከማሰብ ባለፈ ድጋፉን እንደሚያጠናክርም አቶ ፍስሃ አስታውቀዋል።

በመጠለያ ጣቢያው የሎጅስቲክ አስተባባሪ ወይዘሮ የሺ ካሴ በበኩላቸው፥ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች የተፈናቃዮችን ችግር ተረድተው እየደረጉት ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩም ወይዘሮ የሺ ጥሪ አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.