Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ማዳን ተቀዳሚ ጉዳያችን አድርገን እየሠራን ነው – የሀይማኖት መሪዎች ፣ አባገዳዎችና ዑጋዞች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪ ህወሓትና ተላላኪዎቹን ለመገርሰስ የማካሄደውን ዘመቻ በመደገፍ ኢትዮጵያን ለማዳን ተቀዳሚ ጉዳይ አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን በድሬዳዋ አስተዳደር የኃይማኖት ተቋማት መሪዎች ፣ አባገዳዎችና ዑጋዞች አስታወቁ።
በአስተዳደር የሚገኙት እነዚህ አካላት በሀገር ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በድሬዳዋ ተወያይተዋል።
ሀገርና ሠላም የሌለው ሰው ምንም ስለሌለው ሀገርን መጠበቅ ቀዳሚ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተሳታፊዎቹ አመልክተዋል።
ሀገርን ለማዳን ከፀሎትና ምህላ በዘለለ አሸባሪዎችን ለመገርሰስ የሚደረገውን ዘመቻ እንዲሳካ ግንባር ድረስ ተጉዘው እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
የወያኔ ወራሪ ኃይል ቤተ እምነቶችንና መስጂዶችን በማፈራረስና ንፁሃንን በመጨፍጨፍ ሰይጣናዊ ተግባራት እያከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።
በመላው ሀገሪቱ የሰይጣን ተግባራትን የሚከውኑ አሸባሪዎችን እንዲጠፉ ሁሉም በፆምና በፀሎት እየተጋ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘመቻው የሞት ሽረት በመሆኑ እስከመጨረሻው ድረስ ወጣቶችን ወደ ግንባር እንዲዘምቱ በማነሳሳት፣ የተፈናቀሉት ወገኖችን በመደገፍና ሠራዊቱን ባለን ሁሉ ከጎኑ በመቆም የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ እየሰራን ነውም ነው ያሉት።
ሁሉም የሚሆነው ሀገር ሲኖር በመሆኑ ሀገርን ከአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ማዳን የመከላከያ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ይህን ተልዕኮ ለማሳካት በምስራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቁስ፣የገንዘብና የሰው ኃይል ማሰባሰብ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ሀገርን ማዳን ከአካባቢ ስለሚጀምር በአንድ መንፈስና ልብ የወያኔን ሀገር አፍራሽ ተላላኪዎች ማፅዳት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቅም ያለው በአቅሙ ፣ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ዕውቀት ያለው በዕውቀቱ ሀገርን ለማዳን እየተሰለፈ ይገኛል፤ ይህም እስከመጨረሻው ድል ድረስ ይቀጥላል ብለዋል።
በውይይቱ የተወሰደው አቋምና እየተሰበሰበ የሚገኘው ድጋፍ የሀገር ለማዳን ወሳኝ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረዋል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.