Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ግጭት የተካሄደው የምርመራ ሪፖርት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት አግኝቷል-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ጋር በጣምራ በትግራይ ግጭት ላይ ያካሄዱት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሪፖርት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ  እንደገለጹት ÷ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ጋር በጣምራ በትግራይ ግጭት ተፈጸሙ በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ አድርገው  ሪፖርቱን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል፡፡

ሪፖርቱንም 16 አገራት፣ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ኃላፊዎችና የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሀገሮች ጭምር ተቀብለውታል ነው ያሉት ዶክተር ዳንኤል።

ሪፖርቱን የተከታተሉት ሀገራት በጥናቱ የተሳተፉ ሁለቱን ተቋማትን ገለልተኛና ተኣማኒ ሪፖርት በማቅረባቸው አመስግነዋል፡፡

የሪፖርቱን ምክር ሃሳብም በግጭቱ የተሳተፉ ወገኖች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.