Fana: At a Speed of Life!

ለሰራዊቱ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን  የድሬዳዋ ባለሃብቶች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ባለሃብቶች የአሸባሪውን ህወሓት ሴራ ለማጋለጥ እና  የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ  የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል፡፡

በመድረኩም  በገንዘብና በአይነት ከምናደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመገኘት ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ባለሃብቶቹ ተናግረዋል፡፡

እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን ያሉት ባለሃብቶች÷ በመጀመሪያው ዙር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 12 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንና  በቀጣይም  የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

የገቢና ሎጀስቲክ ኮሚቴ በማቋቋም በሁሉም የአስተዳደሩ ቀበሌዎች ለመከላከያ ሠራዊት በገንዘብና በአይነት ድጋፎችን የማሰባሰቡ ሂደት መቀጠሉም ተመላክቷል፡፡

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር÷ በአስተዳደሩ ህውሓትን ለመደገፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ250 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንስተዋል፡፡

ከተማዋ ካላት የመልካ ምድር አቀማመጥ አንፃር እነዚህ አካላት እኩይ ሴራቸውን ለማስፈፀም አቅደው መንቀሳቀሳቸውን የገለፁት ከንቲባው÷  ይህ ከመሆኑ በፊት ባለሃብቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም የሱፍ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስም ቢሆን እጓዛለሁ ያለውን ህወሓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር የድሬደዋ ባለሃብቶች ብዙ  ይጠበቅበቸዋል ብለዋል።

ጁንታው በበትረ ስልጣን ላይ በነበረት ጊዜ በድሬደዋ ላይ የተለያዩ አሻጥሮችን ከመስራቱም ባሻገር ለዘመናት በመቻቻል የቆየውን የነዋሪዎችን የአብሮነት እሴት ለመሸርሸር ያልፈነቀለው ድንጋይ እዳልነበረ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለማፍረስ ጁንታውን እንደ እጅ መጠምዘዟ እየተጠቀሙበት የሚገኙት ምዕራባዊያን ሊያውቁት የሚገባቸው እኛ የአባቶቻችን ልጆች መሆናቸውን ነው ያሉት ደግሞ የከተማው ባለሃብቶች ናቸው።

የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ መንግስት እየወሰደ ያለውንም  እርምጃ አድንቀዋል።

ሃብትና ንብረት ሊኖር የሚችለው ሀገር ስትኖር ነው ያሉት ባለሀብቶቹ÷ ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ጥረት በገንዘብና በአይነት ከሚያደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ግንባር በመገኘት ለመዋጋት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.