Fana: At a Speed of Life!

እኛ ለተፋሰሱ አገራት ቀና አመለካከት አለን እነሱ ግን ስለእኛ ግድ የላቸውም-ኡስታዝ ጀማል በሽር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)ኢትዮጵያውያን ለአባይ ተፋሰስ አገራት ቀና አመለካከት አለን እነሱ ግን ስለእኛ ግድ የላቸውም ሲሉ በግድቡ ዙሪያ የማህበረሰብ አንቂ የሆኑት ኡስታዝ ጀማል በሽር ተናገሩ

የማህበረሰብ አንቂው  ከፋና ብሮደካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥እውነት ስላለኝ ብቻ በአባይ ጉዳይ ከአረቡ ዓለምና ከተፋሰሱ አገራት ጋር የማድረገውን ክርክር አላቆምም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እኛ ስለ አረቡ ዓለም እና ስለ ተፋሰሱ አገራት ቀና አመለካከት አለን እነሱ ግን የእኛ ጉዳይ ግድ አይሰጣቸውም ብለዋል ኡስታዝ ጀማል በሽር፡፡

የተፋሰሱ አገራትና የአረቡ ዓለም 85 ከመቶ የሚሆነው የአባይ ወንዝ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ እንደሆነ እያወቁ በግድቡ ዙሪያ የተሳሳቱ ትርክቶችን በመፍጠር ሲያሰራጩ መቆየታቸውንም ገልፀዋል፡፡

በተለይ ግብፅ በግድቡ ዙሪያ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨች መሆኑንና መረጃዎችን እየተከታተሉ እውነታውን በማሳየት ላይ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

ግድቡን በተመለከተ ኢትዮጵያውያን አረብኛ ተናጋሪ አለመሆናቸው በጉዳዩ ዙሪያ ከተፋሰሱ አገራት የሚነሱ የዲፕሎማሲ ጫናዎችን ለመመከት አስቸጋሪ እንደነበር ጠቅሰው እሳቸው እና ሞሃመድ አል አሩሲ በግድቡ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ተሳታፊ መሆናቸው  ጫናውን በተወሰነ መልኩ መቀነስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

እስካሁን በግድቡ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው የድፕሎማሲ ስራ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሲካሄድ እንደነበረ የገለፁት ኡስታዝ ጀማል በቀጣይ በመንግስት ደረጃ በተደራጀ መልኩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት እንደሚያስፈልግ ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

በአብረሃም ፈቀደ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.