Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ እና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን ለመፍታት በ85 ሚሊየን ዶላር የመልሶ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን ለመፍታት በ85 ሚሊየን ዶላር የመልሶ ግንባታና አቅም የማሳደግ ፕሮጀክት ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው ÷ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በ50 ኪ.ሜ ራዲየስ በሚገኙ ከተሞች ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

በዚህም በመዲናዋ እና አካባቢው የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ችግር ለመፍታት በ85 ሚሊየን ዶላር የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮች እርጅና ምክንያት የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር ለመፍታት የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ከሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ የትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ ቻይና ኤሌክትሪክ ፓወር ኢኩፕመንት ቴክኖሎጂ እና ቻይና ናሽናል ሄቪ ማሽነሬ ኮርፖሬሽን በተባሉ የቻይና ተቋራጮች እየተገነባ መሆኑ በመግለጫው ተመልክቷል።

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 85 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት በብድር ተገኝቷል፡፡

ከዚህ ውስጥ 60 ነጥብ 64 ሚሊየን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና 24 ነጥብ 46 ሚሊየን ዶላር ከጃፓን መንግስት በብድር መገኘቱ ተገልጿል፡፡
ግንባታውን በሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።

በፕሮጀክቱ 625 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታና 266 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ተከላ የሚከናወን ሲሆን ÷ አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ከ35 በመቶ በላይ መድረሱ በመግለጫው መጠቀሱን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.