Fana: At a Speed of Life!

ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች  በግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት የሚሆን ስንቅ እያዘጋጁ ነው፡፡

የሸንኮር ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ጌጤነሽ ሮባ÷የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር መስዋዕት እየከፈሉ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት ስንቅ እያዘጋጀን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪም በራሱ ተነሳሽነት በነቂስ በመውጣት የዳቦ ቆሎ፣ በሶና ሌሎች ስንቅ እያዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላዋ የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ሳሚያ ያሲን በበኩላቸው ÷በተለይም በአሁኑ ጊዜ ከውስጥና በውጪ የተከፈተብንን ጦርነትና ጫና ለመመከት  አንድነታችንን በማጠናከር ከመንግስት ጎን መቆም ይኖርብናል  ነው ያሉት፡፡

ከምንም በላይ የሀገር ህልውና ይቀድማል፤ ለዚህም በአሁኑ ወቅት በግንባር ተገኝተው እየተዋደቁ ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት የሚሆን ስንቅ እያዘጋጁ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የአባድር ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ መሊካ አሊም በቀጣይ በአሸባሪው ህውሓትና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ ሀገር የማፍረስ ሴራን ለመቀልበስ በሚከናወኑ ተግባራት ድጋፋቸውን አጠናክረው  እንደሚቀጥሉ  ተናግረዋል፡፡

ሌላኛዋ የጅኔላ ወረዳ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ስንዱ ዘነበ ሰራዊቱን ከመደገፍ ባለፍ ሀገሬን ለመታደግ መዝመት ካለብኝ ያለምንም ማመንታት እዘምታለሁ ብለዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት ህዝቡ ሰራዊቱን መደገፍ እና የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ ቀናትም ከስንቅ ዝግጅት ጎን ለጎን ሌሎች ድጋፍችንም ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.