የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ለህልውና ዘመቻው 143 ሚሊየን ብር ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ አስተዳደሩ ለህልውና ዘመቻው የሚውል 200 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ብርሃን ንጉሴ ገለጹ፡፡
በሀብት ማሰባሰብ ሂደቱ በከተማ ደረጃ 143 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡
ከ 20 ሺህ ኩንታል በላይ ደረቅ ሬሽን ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ15 ሺህ በላይ ኩንታል በአይነት መሰብሰቡንም ተናግረዋል፡፡
ህወሓትን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት÷ በአራት ግንባሮች 30 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መላኩንም አብራርተዋል፡፡
ባለሀብቶች ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉት ድጋፍና ተሳትፎ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል ያሉት ኃላፊዋ÷ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የስንቅ ዝግጅቱ በተጠናከረ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ÷ የከተማው ህዝብ ለህልውና ዘመቻው እያደረገ ያለውን ድጋፍ አስመልክቶ ምስጋና አቅርበዋል።
በሶስት ቀናት ውስጥ በተደረገ የሀብት ማሰባሰብ 17 ሰንጋ፣ 12 በግና ፍየል፣ 4500 ደርዘን ውሃና፣ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ስንቅ መሰብሰብ እንደተቻለ ከንቲባው ገልጸዋል።
አሸባሪው ቡድን ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ የከተማው ማህበረሰብ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።
በሰላም አስመላሽ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!