Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ በአዲስ አበባ የሽብር ቡድኑ የሕወሓትን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት በወንጀል መከላከልና ምርመራ ረገድ በተሰሩ ተግባራትና በተካሄደው ኦፕሬሽን ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ÷ ፖሊስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የማስፈጸሚያ አደረጃጀት በመፍጠር አባላቱ አዋጁን በሚገባ እንዲያውቁት ከማድረግ ጀምሮ ሕዝብና ፖሊስን አስተባብሮ ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

ከተራ ሌብነት ጀምሮ ዜጎችን እየገደለና እያሰቃየ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱት እንደ ሸኔ ፣ የቅማንትና የጉምዝ ታጣቂዎችን አስተባብሮ ሽብሩን ወደመሃል ሀገር ለመሳብና አዲስ አበባ ዙሪያ ለማድረግ እየሠራ ነውም ብለዋል።

ለዚህም በከተሞች ውስጥ ተመሳስሎ በመግባት ሙከራ እያደረገ ነው ያሉት ጀነራሉ ÷ እንቅስቃሴውን ለመግታት የተለያዩ የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ ሪፐብሊካን ጋርድ እና የደህንነት መሥሪያ ቤቱን ጨምሮ እየሠሩ ነው ብለዋል።

በዚህም የሽብር ተልዕኮውን ማስፈፀሚያ የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦች፣ አሳሳች መረጃዎች የተለያዩ የፀጥታ አስከባሪ አባላት አልባሳትን ሲያሰፉ እና ሲያዘጋጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥም የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል፣ የአፋር ክልል ልዩ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የማረሚያ ቤት ደንብ ልብሶችን ጨምሮ ወታደራዊ ማዕረጎች በሀሰት ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል ማለታቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.