በህልውና ዘመቻው መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን የዳያስፖራ ምክር ቤት አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአገር ውስጥ ጀምሮ እስከ ውጭ አገራት ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ለመቀልበስ ዳያስፖራው ማህበረሰብ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ምክር ቤት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ዋና አስተባባሪ አቶ አለባቸው ደሳለኝ÷ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀይ ካርድ የመዘዙበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በተለያየ የዓለም ክፍል ያለው የዳያስፖራው ማህበረሰብም የመከላከያ ሠራዊቱን ለመደገፍ እንዲሁም የታሪክ ግዴታውንና ብሄራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ከአሁን በፊት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ይህንኑ ተነሳሽነት ከፍ በማድረግ ከአገር ውስጥ ጀምሮ እስከ ውጭ የዓለም ክፍል ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ለመቀልበስም በዝግጅት ላይ ይገኛል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!