Fana: At a Speed of Life!

ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንዲቋቋሙ የሚያስችል ድጋፍ ይደረግላቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበለጸጉ አገራት እና የግል ባለሐብቶች ታዳጊ አገራት እየተባባሰ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መቋቋም ይችሉ ዘንድ ከ750 ሚሊየን ዶላር በላይ ለመለገስ ቃል ገቡ፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይም ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ 351 ሚሊየን ዶላሩን ለመስጠት ቃል የገቡት አካላት መለየታቸው ነው የታወቀው፡፡

አሜሪካ እና ካናዳ ለመጀመሪያ ጊዜ የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድተው ታዳጊ አገራቱን ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

የአውሮፓ ህብረት 116 ሚሊየን ዶላር፣ ጀርመን 58 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም አሜሪካ 50 ሚሊየን ዶላር በአየር ንብረት ለውጡ ምክንያት ተጽዕኖ ለሚደርስባቸው ታዳጊ አገራት ለመለገስ ቃል የገቡ እና ከፍተኛ ገንዘብ በመለገስ የአንበሳውን ድርሻ የወሰዱ አገራ ሆነዋል፡፡

የገንዘቡ አሰባሳቢ የቦርድ ሊቀመንበር ማቲያስ ብሮማን ÷ ለለጋሽ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የተለያዩ አገራት መንግስታት እና የግል ባለሐብቶች ይለግሳሉ ብለው እንደሚጠብቁም እምነታቸው ገልጸዋል፡፡

የሚለቀቀውን ገንዘብ የሚያሰባስብ አካል የተቋቋመው በፈረንጆቹ 2001 ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ላይ ታዳጊ አገራትን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ ለመታደግ ታላሚ በማድረግ በተደረሰ ስምምነት ነው፡፡

በገንዘቡ ከ100 በላይ አገራት እና 19 የሚደርሱ ደሴቶች እንዲሁም 33 በዝቅተኛ የኢኮኖሚ የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.