Fana: At a Speed of Life!

ጠላት አማራን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ካላፈረሰ አያርፍምና ሁላችንም በአንድነት እንነሳ – አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡

ሃላፊው በዚህ ወቅት እንደገለጹት ÷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አሁን ያለንበት የህልውና ዘመቻ በድል ለማጠናቀቅ እና ከጦርነት ውጭ ያሉ አካባቢዎችን ለመከላከል የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የህልውና ዘመቻውን የሚያደናቅፉና በጦር መሳሪያም ሆነ በተለያየ መንገድ አሸባሪውን የሚደግፉ የመለየትና ትክክለኛ መረጃ የመያዝ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በዚህም ጥንቃቄ በማድረግ የህልውና ዘመቻውን በተለያየ መንገድ የሚያደናቅፉ አካላትን የመያዝ ስራ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው ዘመቻውን በቀጥታ ከሚደግፉ ተቋማት ጋር በተያያዘም የጸጥታ ተቋማት፣ የጤና ተቋማት፣ ግብርና እና ሌሎችም ክፍት ሲሆኑ ትምህርት በከፊል እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

ሰዓት እላፊ ገደቡም ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ÷ ማህበረሰቡም ለህልውና ዘመቻው እያደረገ ያለው ድጋፍ ይበል የሚያሰኝ ነውም ብለዋል አቶ ግዛቸው፡፡

አሁንም ህዝቡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አክብሮ እንዲሁም የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት ከመንግስት ጋር በመሆን እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ በክልሉ መንግስት የተደረገው የክተት ጥሪ የተለየና ወደ ድል የሚያመራ እንዲሁም የሚያድግ መሆኑንም አውስተዋል።

አያይዘውም የህልውና ዘመቻውን ደጋፊ የሆኑ የግዴታ ጥሪዎች መካተታቸውን ጠቅሰው፥ ሁሉም ነገር ወደህልውና ዘመቻው መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም የመንግስት ተቋማት (ከክልል ቢሮዎች ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉት) አቅርቦት ላይ ኮታ ተጥሎ እየሰሩ ነውም ተብሏል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች ከወታደራዊ አመራሮች ጋር በጥምረት እየሰሩ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሃላፊው ÷ ግንባር ድረስ በመሄድም ዘመቻውን እያገዙ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

በሰላም አስመላሽ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.