Fana: At a Speed of Life!

የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ የተጀመሩት ስራዎችን ለማፋጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ የተጀመሩት ስራዎችን እንዲፋጠኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር አብርሃም በላይ ገለጹ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር አብርሃም በላይ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ ሀገራችን በስፔስ ምህንድስና የጀመረቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት የተጀመሩ ስራዎች እና ከሪሞት ሴንሲንግ ሳተላት በተጨማሪ በኮሚኒኬሽን ሳተላይት ባለቤትነት ዙርያ የተጀመሩት ስራዎች እንዲፋጠኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነችው ETRSS-1 ሳተላይት የምስል መረጃዎች በፍጥነት ጥቅም ላይ ለማዋል ከተጠቃሚ አካላት ጋር ግንኙነት በመጀመር ተደራሽ ለማድረግ እንዲሰራም አቅጣጫ መስጠታቸውም ነው የተገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል የማልት ሂደቱን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማቀናጀት እንዲሰራ፣ የተጀመረው የሳተላይት ፋብሪካ፣ የመገጣጠሚያና ፍተሻ ማዕከል፣ የስፔስ ኢንዳስትሪውን ለመምራት የሚያስችል የስፔስ ለብራቶሪ እንዲገነባ እንዲሁም ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የተሻለ ልምድ ካላቸው የውጭ አካላትና ዳያስፖራዎች ጋር እንዲሰራም አቅጣጫ መስጠታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.