ስፓርት

አስቶንቪላ ስቲቨን ጄራርድን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

By ዮሐንስ ደርበው

November 11, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ አስቶንቪላ ዲን ስሚዝን ካባረሩ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለማግኘት ፍለጋ ላይ ቆይተዋል።

በዛሬው እለትም የቀድሞውን የሊቨርፑል አማካይ ስቲቨን ጄራርድ አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

የስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ አሰልጣኝ የነበረው ጄራርድ አስቶንቪላን በሁለት አመት ተኩል ኮንትራት በአሰልጣኝነት ተረክቧል።

የ41 አመቱ እንግሊዛዊ እና የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ በሬንጀርስ ቆይታው ከቡድኑ ጋር የስኮቲሽ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

ከጄራርድ ቅጥር ጋር በተያያዘ አስቶንቪላ ለስኮትላንዱ ሬንጀርስ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ካሳ እንደሚከፍል ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!