Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ ተቸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዴቪድ ስታይንማን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ በመተቸት ደብዳቤ ጽፏል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዴቪድ ስታይንማን አሜሪካ በኢትዮጵያ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ እያራመደች ያለውን ፖሊሲ አሳፋሪ ሲል ጠርቶታል።

ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ቀርቦ የነበረው ዴቪድ ስታይንማን በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ጀፍር ፌልትማን በጻፈው ደብዳቤ፥ የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በቁርጠኝነት መቆም እንዳለበት እና በሰብአዊ አቅርቦት፣ በሰብአዊ መብት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይም አዲስ ስምምነት እንዲያደርግ ጠይቋል።

በህዝብ የተመረጠን መንግስት እና አምባገነኑን ህወሓት መልሶ ለማምጣት የሚታገልን አሸባሪ ቡድን እኩል መመልከት ችግሩን ከማባባስ ውጭ የሚያመጣው ፋይዳ የለውም ሲል የአሜሪካን አካሄድ ተችቷል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩ ሁነቶችን በደብዳቤው ያነሳው የምጣኔ ሃብት ባለሙያው፥ ህወሓት ኢትዮጵያን እያስተዳደረ በነበረበት ጊዜ ከህወሓት ጋር ሲሰሩ የነበሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማቶች አሁንም ህወሓት የፈጠረውን ግጭት ሚዛናዊ ሆነው ይፈታሉ ብሎ መጠበቅ ልክ አይደለምም ብሏል፤

በአንድ ወቅት ቢንላደንን ሲያሞግሱ የነበሩ ዲፕሎማቶች በአሜሪካ እና አልቃይዳ መካከል ያለውን ጦርነት ላሸማግል ቢሉ አሜሪካ ትፈቅዳለች ወይ? ብሎ ከጠየቀ በኋላ የኢትዮጵያ ሁኔታም በዚህ መንገድ ሊታይ እንደሚገባ በመግለጽ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያንም ለአሜሪካ እና ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ያላቸው እይታ ይህንን ያሳያል ይላል።

ሌላው የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ያልተረዱት የህወሓት ባህሪ ደግሞ በህወሓት ቁጥጥር ስር ባለው “የሽግግር መንግስት” ሽፋን ኢትዮጵያን የመቆጣጠር አላማ በመያዝ በአገር አቀፍ ደረጃ አምባገነናዊ አገዛዛቸውን እና የሙስና ወንጀሉን ለማስቀጠል እንደሚሰራም ይጠቅሷል።

ህወሓትም እንደመንግስት አገርን ያስተዳድር በነበረ ጊዜም ይህንን የከፋፍለህ ግዛ እና የማተራመስ ስልት እስከ ውድቀቱ እለት ድረስ ይጠቀምበት እንደነበር ሊታወቅ ይገባል ነው ያለው።

ድርድር እና ውይይት በወያኔ አሰራር የሚያስኬድ አይደለም፤ ህወሓቶች የራሳቸውን ግላዊ ጥቅም እስካስከበረ ድረስ እና ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት እንደ መወጣጫ መንገድ ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ፤ ይህ ደግሞ ብዙሃኑን ኢትዮጵውያን የሚጎዳ እና አግባብነት የሌለው ነው ይላል ዴቪድ ስታይንማን።

የህወሓትን የማተራመስ ዘመቻ ማስቆም ካልተቻለ በስተቀር አሁን እየተኬደበት ያለው መንገድ የህወሓት አቅምን ጠብቆ የሚያቆይ የሰላም ድርድር የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና መረጋጋት ስጋት ላይ እንደሚጥልም ይጠቁማል።

እውነታው ግን አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አውሮፓውያን የሚያንጸባርቋቸው ሃሳቦች ለህወሓት ያላቸውን አድሏዊነት የሚያንጸባርቅ ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈም በትግራይ ለተፈጠረው የእርዳታ አቅርቦት መቋረጥ ምክንያቱ ህወሓት መሆኑን በመገንዘብ ህወሓት ወራራውን እንዲያቆም ማድረግና ለኢትዮጵያ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አለማቋረጥ መፍትሄ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.