የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለአንድ ሳምንት ተራዘመ

By ዮሐንስ ደርበው

November 11, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ በቀጣይ አንድ ሳምንት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚካሄድ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

 

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የደቡብ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ባዉዲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ለ5 ተከታታይ ቀናት የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦችና ተቋማት እንዲያስመዘግቡ ዉሳኔ ቢተላለፍም÷በነዚህ ቀናት መዝግቦ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ከነገ 03/03/2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ለመጨረሻ ጊዜ ይካሄዳል ብለዋል።

በመሆኑም እስከአሁን የጦር መሳሪያ ያላስመዘገቡ ግለሰቦችና ተቋማት በቀጣይ አንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ በቅርበት ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ መቅረቡን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል።