ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከሃላፊነት አነሳች

By Tibebu Kebede

February 11, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ አልተቆጣጠሩም ያለቻቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነት አሰናብታለች፡፡

በአሁን ሰዓት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰው ኮሮና ቫይረስ በቻይና ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው ተሰናብተዋል፡፡

የሁቤይ ቀይ መስቀል ምክትል ዳይሬክተር የመጣውን እርዳታ በአግባቡ ካለማድረስ ጋር በተያያዘ  ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ነው የተነገረው።

በተመሳሳይ የሁቤይ ጤና ኮሚሽን የፓርቲው ጸሐፊ  እና የጤና ኮሚሽኑ ሃላፊ ከሃላፊነታት  ተነስተዋል።

በሁቤይ አውራጃ ትላንት ብቻ 103 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ÷ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ደግሞ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 16 ደርሷል።

ነገር ግን በየቀኑ በበሽታው የሚያዙ የአዲስ ሰዎች ቁጥር ግን ካለፈው ጋር ሲነፃፀር 20 በመቶ ቀንሷል ነው የተባለው ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!https://t.me/fanatelevision