የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚውል 200 ሚሊየን ብር አጸደቀ

By Alemayehu Geremew

November 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ካቢኔ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ የሚውል 200 ሚሊየን ብር አፀደቀ፡፡

ካቢኔው ገንዘቡን ያጸደቀው ዛሬ በጎዴ ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው፡፡

ካቢኔው በተለያዩ ወቅታዊ ፣ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን፥ በተለይ በክልሉ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች አስቸኳይ ምላሽ መስጠት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በስፋት መምከሩን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።