የሀገር ውስጥ ዜና

ሁዋዌ በቴክኖሎጅው ዘርፍ የትብብር ስራዎቹን የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

By Meseret Awoke

November 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ በኢትዮጵያ ሲያከናውናቸው የነበሩ ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ የትብብር እና የድጋፍ ስራዎችን የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው በልዑካኑ በኩል ገልጿል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ የሁዋዌ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ሁዋዌ በቴክኖሎጂ ዘርፍ አበረታች ስኬቶችን እያስመዘገቡ ካሉ ድርጅቶች በግንባር ቀደምነት እንደሚጠቀስ ጠቁመዋል።

የነበሩት ሂደቶችን በማድነቅ በቀጣይ በተለይ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሎሎች ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ስምምነቶችን በማደስ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የትብብር ስራዎችን በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

የሁዋዌ ዋና ዳይሬክቴር ጀሪ ቼን በበኩላቸው ከአሁን ቀደም በጋራ የተከናወኑ ተግባራትን በአድናቆት እንደሚመለከቱ ገልጸዋል።

በቀጣይም የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስራዎችን ለማከናወን የትብብር መስኮችንና ዘርፎችን በመለየት በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!