Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለሰራዊቱ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለአገር መካከያ ሰራዊት 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሴት ሰራተኞችም ለሰራዊቱ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን የተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ለመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል።

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ተመስገን ጋሮማ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፥ የድርጅቱ ሠራተኞች ከዚህ ቀደምም የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሰራዊቱ ለግሰዋል።

በቀጣይም የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የአገልግሎቶችና መልካም አስተዳደር ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አለምፀሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፥ ፅህፈት ቤቱ ለህልውና ዘመቻው የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

የፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ከዚህ ቀደም የደም ልገሳ ከማድረግ ባሻገር ከደመወዛቸው የ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም ምግብ ነክ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመው፥ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ ለሰራዊቱ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ መሆኑንም ገልፀዋል።

ኅብረተሰቡም የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.