Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለማገዝ በሚችሉት አቅም ሁሉ ከጎኑ እንደሚቆሙ የወላይታ ዞን መንግስት ሠራተኞች ተናገሩ።

ሠራተኞቹ የሀገርና የህዝብ ህልውና ለማስጠበቅ ከጠላት ጋር በግንባር እየተፋለመ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም በመለገስ ድጋፍ አድርገዋል።

በደም ልገሳው የተሳተፉት የዞኑ አስተዳደር ሠራተኛ አቶ ፍቅሬ ቶማስ በበኩላቸው ÷ የደም ልገሳው ለሀገር ክብርና አንድነት የምንከፍለው ትንሹ መስዋዕትነት ነው ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊትን መደገፍ ሀገርንና ቤተሰብን መደገፍ መሆኑን ገልጸው ÷ ለሠራዊቱ በሚደረግ ድጋፍ በተለያየ መንገድ እገዛ እያደረጉ መሆኑንና ወደፊትም ድጋፉን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ወንድሙ ኃይሌ “ለእኛ ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ላሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ያለኝን አጋርነት ለማሳየት ደሜን ለግሻለሁ” ብለዋል።

“ሁሉም የሚያምረው በሀገር ነው” ያሉት አቶ ወንድሙ ÷ “እናት ሀገሬን ለመጠበቅ ከደም ልገሳና የገንዝብ ድጋፍ ባለፈ ህይወቴን መስጠት ካለብኝ እሰጣለሁ” ነው ያሉት።

የመከላከያ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያን ክብር ለማስጠበቅ እየከፈሉት ያለውን መስዋዕትነት ታሪክም ትውልድም አይረሳውም” ያሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ያሲን ያና ናቸው።

“እነሱ እየከፈሉት ላሉት መስዋዕትነት ደም መለገስና ስንቅ ማቀበል ብቻ በቂ አይሆንም” ብለዋል።

ለዚህም ሠራዊቱ እያደገ ላለው ተጋድሎ ግንባር ድረስ ሄደው ከጎኑ ለመሰለፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው ÷ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ለሀገር ህልውናና ክብር ሲል በዱር በገደሉ ከጠላት ጋር እየተዋደቀ ነው ብለዋል።

ከአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ጋር በሚያደርገው ተጋድሎም እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የህዝብ ሰራዊት መሆኑን እያረጋገጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከምንም በላይ የሀገሬና የህዝቤ ደህንነት ይቀድማል በሚል ውሎ አዳሩን የጠላትን አንገት እየተናነቀ ላለው ለዚህ ሠራዊት ህዝቡ ደጀንነቱን በተለያየ መንገድ እያሳየ መሆኑን ነው የገለጹት።

እየከፈለ ላለው መስዋዕትነት ክብር ለመስጠትና አጋርነቱን ለማሳየት የዞኑ ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸወን ቀደም ሲል መለገሳቸውን ጠቅሰው ÷ አሁንም ደማቸውን በመስጠት ዳግም አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸውን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ የዞኑ ሠራተኛና ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.