Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

 አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል።
በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጀጃ ባህሪ ግንብ ቀበሌ የዘማች ቤተሰቦችን የደረሱ ሰብሎች ሰብል በመሰብሰብ ደጀንነታቸውን ማስመስከራቸውን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የግብርና ኮሌጅ የተፈጥሮ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህርና የመርኃግብሩ አስተባባሪ መምህር ፍቃዱ ሀብቴ ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.