Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ በማይጠብሪ ግንባር ለሚዋደቁ ጀግኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከ530 ሺህ ብር በላይ ግምት የሚያወጡ 27 በሬዎችን በማይጠብሪ ግንባር ለሚዋደቁ ጀግኖች ድጋፍ አደረገ።
አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙ የወገን ጦር ሰራዊት ማበረታቻ የተለያየ የስንቅ ድጋፍ ለጦሩ እንዲሰጥ ተደርጓል ተብሏል።
በግንባር በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ፥ የከተማዋ ነዋሪዎች ሀብት የማሰባሰብና ስንቅ የማዘጋጀት ተግባር በተቀናጀ መንገድ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ ከባለሀብቶችና ከነዋሪዎች የተገኘ መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፥ የመንግስትን ጥሪ ተቀብሎ በርካታ ሰው ወደ ህልውና ዘመቻው እየተመመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው ህወሓት ሙሉ በሙሉ እስከሚደመሰስ ድረስ አሁን የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በላቀ የህዝብ ተሳትፎ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።
በተያያዘ የአዘዞ ደብረ ሰላም ሎዛ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዘዞና ልጆቿ በጎ አድራጎት ማህበርና አዘዞ ጠዳ ሴቶች ሊግ 1 ሚሊየን 560 ሺህ ብር የሚገመት የአልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በምናለ አየነው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.