Fana: At a Speed of Life!

“ህይወቱን ሳይሰስት ለኛ መኖር ለሚዋደቀው ሠራዊት ምግብ ማቅረባችን ከሚጠበቅብን ጥቂቱ ኃላፊነታችን ነው”- የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው ህወሓትን ለመደምሰስ ግንባር ለተሰለፈው ሕዝባዊ ሠራዊት ደጀን ሆነው እየሠሩ መሆናቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የቀወት ወረዳ ነዋሪዎች አንድ ህይወቱን ሳይሰስት እየሰጠን ላለው ሠራዊት ደጀን መሆናችን ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም ብለዋል።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ለሠራዊቱ ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ስንቅ ከማቀበል ባለፈ በግንባር ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሽብርተኛው ህወሓት እንደ ሕዝብ ሊያጠፋን መምጣቱን በውል መገነዘብ ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ ከተደቀነብን የህልውና አደጋ ለመውጣት በሕዝብ ማዕበል ጠላትን ማጥፋት ይገባል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የቀወት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተሾመ ሸዋዬ ነዋሪው ለሠራዊቱ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ነው የጠየቁት።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.