የሀገር ውስጥ ዜና

“ህይወቱን ሳይሰስት ለኛ መኖር ለሚዋደቀው ሠራዊት ምግብ ማቅረባችን ከሚጠበቅብን ጥቂቱ ኃላፊነታችን ነው”- የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው ህወሓትን ለመደምሰስ ግንባር ለተሰለፈው ሕዝባዊ ሠራዊት ደጀን ሆነው እየሠሩ መሆናቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የቀወት ወረዳ ነዋሪዎች አንድ ህይወቱን ሳይሰስት እየሰጠን ላለው ሠራዊት ደጀን መሆናችን ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም ብለዋል።