Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች የህወሓትና ሸኔን እኩይ ድርጊት አወገዙ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምእራብ ኦሞ ዞን የህልውና ዘመቻን የሚደግፍ እና የአሸባሪዎቹን የህወሓትና ሸኔን ተግባር የሚቃወም ሰልፍ በጀሙ ከተማ ተካሄደ ፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን እያደረሰ የሚገኘውን ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት አውግዘዋል።

በሰልፉም እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ፣ የአድዋ ታሪክ በጁንታው መቃብር ላይ ይደገማል የሚሉና አሁን ላይ እየተደረገ ያለውን የውጭ ሚዲያዎች ሀሰተኛ ዘመቻ የሚያወግዙ መልዕክቶችን ይዘው ወጥተዋል፡፡

በሰልፉ ላይ የምዕራብ ኦሞ ዞንና የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት መገኘታቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌዥን ድርጅት ዘግቧል::

በተመሳሳይ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሚቃወምና መከላከያን የሚደግፍ ሰልፍ በአማሮ ወረዳ ኬሌ ከተማና በዳውሮ ዞን ተካሂዷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.