የብድር አሰጣጥ ስርዓቱ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተስተካክሏል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፋት ዓመታት ከነበረበት ችግር አገግሞ ለውጥ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
የልማት ባንክ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩም ባንኩ ትርፋማ ሆኖ መቀጠሉ፣ ጤናማ ያልሆነ የብድር ምጣኔው እየቀነሰ መገኘቱን እና ከዕቅድ ጋር ሲነጻጸር በብድር የተሰበሰበው ገንዘብ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየቱን አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡
የባንኩን ቢዝነስ ሞዴል ለማስተካከል እና የብድር አሰጣጥ ሥርዓቱ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ማስተካከያ ማድረጉ እና የባንኩ የፋይናንስ ጤናማነት እየተሻሻለ መምጣቱንም ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ለማድረግና ተቋሙ ዘላቂ የገንዘብ ምንጭ እንዲኖረው ለማስቻል፣ ጤናማ ያልሆነ ብድር ምጣኔውን እንዲቀንስ፣ የፕሮጀክቶች ክትትል እንዲጠናከር እንዲሁም ትርፋማነቱን ለማስቀጠል እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን በማቅረብና የቅርንጫፍ አከፋፈቱን ፍትሃዊ በማድረግ ላይ የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!