Fana: At a Speed of Life!

በዋግ ኽምራ ዞን የሽምቅ ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ዞን ሽብርተኛው ህወሓት የከፈተውን ወረራ ለመቀልበስ የወገን ጦር ዳህና እና ዝቋላ በተባሉ ሁለት ግንባሮች በወራሪው ሀይል ላይ የተጠናከረ የማጥቃት እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ከአካባቢው ምንጮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ወራሪዎቹ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ድባቅ እየተመቱ የተገኙ ድሎችም ተመዝግበዋል።

በሁለቱም ግንባሮች ሽብርተኛውን እየተፋለሙ ያሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ ፣ ሚሊሻዎች እና ሌሎቸ ታጣቂ ሀይሎች ሲሆኑ ፥ የጋራ ግንባር ፈጥረው ድል እያስመዘገቡ ነው፡፡

በዋግ ኽምራ ግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ያለው የወገን ሀይል የከፈተው የሽምቅ ውጊያ ከቆዝባ ወደ ሶስት አምባ እና ሚዝርብ የሚባሉ ቦታዎች የተሻገረ ሲሆን ውጊያው አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ከወገን እየተወሰደባቸው ባለው የማጥቃት እርምጃ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየገጠማቸውና ተከታታይ ድል እየተመዘገበ መሆኑን የአካባቢው ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

የወገን ሀይል በጁንታው ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ ስሬል እና ፀመራ የሚባሉ ቦታዎች ላይ የአገው ሸንጎ ታጣቂዎችም ጭምር የጠላትን እኩይ ዓላማ በመደገፍ ተቀናጅተው ለመመከት ቢሞክሩም ከሽብርተኛው ጋር እንደተመቱ ተጠቁሟል።

የሽብርተኛው ቡድንና ተላላኪዎቹ የወገንን ሀይል መቋቋም አቅቷቸው የአርሶ አደሩን እህል ከአውድማ ጭምር እየዘረፉና እየጫኑ ለማሸሽ እየሞከሩ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.